“አጫይላ” የተሰኘ የህጻናት የአፋ ኾንሶ ፕሮግራም ሥርጭት በFM 90.9 ሊጀመር ነው

“አጫይላ” የተሰኘ የህጻናት የአፋ ኾንሶ ፕሮግራም ሥርጭት በFM 90.9 ሊጀመር ነው

“አጫይላ” የተሰኘ የህጻናት የአፋ ኾንሶ ፕሮግራም ሥርጭት በFM 90.9 ሊጀመር ነው

የደቡብ ራድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በዓይነቱ ልዩ የሆነና እያዝናና የሚያስተምር የህጻናት ፕሮግራምን ከአርባምንጭ ኤፍ ኤም ጣቢያው ለኮንሶ ህጻናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በFM 90.9 ማሠራጨት ሊጀምር መሆኑን፣ በደቡብ ራድዮና ቴሌቪዥን የሚድያ ባለሙያ የሆኑት ጋዜጠኛ አማሮ አርሳባ ለኮንሶ ዜና ገለጹ።

ፕሮግራሙ “አጫይላ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ስነ ምግባርን፣ መቻቻልን፣ ችግር ፈቺነትን፣ ዕርቅን፣ ከባድ ሁኔታን መቋቋም መቻልን፣ ራስን መቆጣጠር መቻልንና ሌሎችም ጠቃሚ የሆኑ እሴቶች በጭውውት መልክ ለልጆች የሚቀርቡበት መርሃ ግብር ነው።

የፕሮራሙ ሥርጭት ዘውትር ማክሰኞ ከጠዋቱ 3፡40 እስከ 4፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ምሽት ከ12፡40 እስከ 1፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ለ20 ደቂቃዎች የሚተላለፍ ይሆናል ተብሏል።

ፕሮግራሙ ከInternational Rescue Committee (IRC) ጋር በመተባባር የሚዘጋጅ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአፋ ኾንሶ ቋንቋ ባለሙያዎች፣ የትምህርት፣ የባህል፣ የሴቶችና ህጻናት ዘርፍ ባለሙያዎች፣ የሚድያ ባለሙያዎች፣ የባህል አባቶችና ከሁሉም የኮንሶ ቀበሌያት የተውጣጡ የህጻናት አሳዳጊዎች በዝግጅትና ግምገማ ሂደቱ ተሳትፈዋል።

ፕሮግራሙ በልዩ ጥንቃቄ የተዘጋጀና በሚድያው ታሪክ በዓይነቱ ልዩና የመጀመሪያው የህጻናት ፕሮግራም ነው ተብሎለታል።

ፕሮግራሙ ከቀረጻ ጀምሮ የአርትዖት ሥራ ተሠርቶ እስኪጠናቀቅ ከ5 ወር በላይ የፈጀ ሲሆን፣ በ20 ተከታታይ ክፍሎች እንደሚቀርብ የአርታዖት ሥራውን የሠሩት ጋዜጠኛ አማሮ አራሳባ ለኮንሶ ዜና ተናግረዋል።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *