
በመጀመሪያ ደረጃ ወንድሜን ተስፋዬ ጫንፋን ስለበጎ ተግባሩ ላመሰግን እወዳለሁ። ስለክርስትና እና ባህል ለውይይት የሚጋብዝ የመነሻ ጽሑፍ ማቅረቡ ልያስመሰግነው ይገባል። በመነሻ ጽሑፉ መግቢያ ላይ እንደ ተገለጸው ወንድማችንን ወደዚህ ዓይነት ውይይት እንዲመጣ ያነሳሳው ገፊ ምክንያት የኮንሶን ባህል ለማስተዋወቅ እየሰራ ባለው ስራ ላይ አንዳንድ ክርስትያን ወገኖች ያንጸባረቁት አሉታዊ አመለካከት ነው።
በመነሻ ጽሑፉ መግቢያ ላይ ስለክርስትና እና ባህል ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች በማንሳት ከአንድ ታዋቅ የክርስትና ስነ-ምግባር መምህር ከነበረ የነገረ-መለኮት ሰው መጽሐፍ አገኘዋቸው ያላቸውን አምስት ሀሳቦች ይዘረዝራል። እንደ ተስፋዬ መረዳት እነዚህ በመጽሐፉ የተዘረዘሩት አምስት ነጥቦች በክርስትና እና በባህል መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሳየት የተቀመጡ ናቸው። ተስፋዬ በመንደሪደሪያ ሀሳቡ ላይ የመጽሐፉ ጸሐፊ ትኩረት አምስቱን ነጥቦች ተጠቅሞ «ክርስትና እና ባህል በአፍርካውያን ዘንድ እንዴት ይታያል የምለውን ነው ለማየት የሞከረው» ይላል።
ምንም እንኳ ለውይይት የምጋብዘው ጽሑፍ የምበረታታ ቢሆንም፤ በእኔ በኩል ውጤታማ እና በአመክንዮ ላይ የተመሰረት ውይይት ለማድረግ አስቀድሞ ወንድማችን ባቀረበው ጽሑፍ ላይ መጥራት ያላባቸው ነገሮች ማጥራት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ለውይይቱ የመነሻ ሀሳብ ለማቅረብ የተጠቀመው CHRIST AND CULTURE በምል ርዕስ የተጻፈው የ H. RICHARD NIEBUHR መጽሐፍ በሁለት መሰረታዊ የተሳሳቱ መንገዶች ተገልጿል (misrepresented)። በነገራችን ላይ ይህ መጽሐፍ ከተጻፈ ግማሽ ምዕተ ዓመት ያለፈው ቢሆንም አሁንም ድረስ ታዋቅና ተጽእኖ ፈጣሪ ነው (1956 እ.እ.አ)።
(1). መጽሐፉ በዋናነት የክርስትና እና የባህልን ግንኙነት አምስት መንገዶች ለመግለጽ አይደለም የተጻፈው። ወንድም ተስፋዬ «Richard niebuhr ”Christ and culture” በሚለው መጽሐፉ ላይ በ5 መንገድ የክርስትና እና የባህልን ግንኙነት አስቀምጧል ።» ብሎ በማለቱ መጽሐፉንም ሆነ ጸሐፊውን አሳስቶ አቅርቧል (misrepresent)::
በመጽሐፉ የምስጋና ገጽ (acknowledgments) ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የመጽሐፉ ትኩረት ቤተ ክርስትያን በታሪክ ውስጥ ጌታዋ ክርስቶስን እና ባህልን በተመለከት ላሉት ልዩ ልዩ ጥያቄዎች እና ተጨባጭ እውነታዎች ምላሽ ለመስጠት ባደረገችው የዘመናት ጥረት ላይ ነው “wrestle of the church with its Lord and with the cultural society”።[1] እንዲሁም በመጽሐፉ ምዕራፍ አንድ መግቢያ ላይ ጸሐፊው ክርስትና እና ባህል በተመለከተ ጉዳዩ “ዘላቅ ችግር”[2] (enduring problem) ነው በማለት ያቀረባቸው አምስት ነጥቦች ወንድም ተስፋዬ እንዳስቀመጠው አምስት የክርስትና እና ባህል ግንኙነት መንገዶች ሳይሆኑ በታሪክ ውስጥ የነበሩ አሁንም የሚታዩ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስትያን ድምጾች ናቸው። ስለዚህ “የክርስትና እና የባህል ግንኙንት” አምስት መንገድ ብሎ ማቅረብ መጽሐፉን እስከተመለከተ ድረስ አሳሳች ይመስለኛል።
(2) ጸሐፊው በመጽሐፉ “ክርስትና እና ባህል በአፍርካውያን ዘንድ እንዴት ይታያል የምለውን” አይደለም “ለማየት የሞከረው”። ይልቁኑ ከጥንት ቤተ ክርስትያን አንስቶ እስከ ዘመናዊው ዘመን ድረስ ያለውን የቤተ ክርስትያን ልምምድ ነው የሚያነሳው እንጂ በአፍርካዊያን ላይ አይደለም ያተኮረው። በየዘመናቱ በጉዳዩ ላይ ትንታኔ የሰጡትን ታሪካዊ ስዎች በብዛት አንስቷል። በመሆኑም ወንድም ተስፋዬ በዝርዝር ነጥቦቹን ስያስቀምጥ እያንዳንዱን ነጥብ አንድ ታሪካዊ ተወካይ ያለው በምመስል መልኩ ማስቀመጡ አሁንም መጽሐፉን እስከተመለከተ ድረስ አሳሳች ይመስለኛል።
የመጽሐፉ ትኩረት ቤተ ክርስትያን በታሪክ ውስጥ ጌታዋ ክርስቶስን እና ባህልን በተመለከት ላሉት ልዩ ልዩ ጥያቄዎች እና ተጨባጭ እውነታዎች ምላሽ ለመስጠት ባደረገችው የዘመናት ጥረት ላይ ነው
መውጫ
ክርስትና እና ባህልን በተመለከተ የግሌን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ነገረ-መለኮታዊ ምልከታ በውይይቱ ለመሳተፍ አቀርባልሁ። ለአሁኑ ግን በዚህ ላብቃ። ወንድም ተስፋዬም በዚህ ጉዳይ ላይ ሀሳቡን አሳስቸ አቅርበ እንደሆነ ልያርመኝ እንደምችል ማሳወቅ እወዳለሁ።
[1] Niebuhr, Christ and Culture, 1.
[2] Niebuhr, Vii.
Niebuhr, H. Richard. Christ and Culture. Text. 1st ed. New York: Harper, 1951.
I think Christianity teach how to find Jesus in the body of Christ. It is all how to live with Christ and it is not about the unique culture. Christ appear in the culture of Jewish and so that lived as per the culture. Think that what happen if Christ would have appeared in the culture of pastoralist in different parts of the world. Would he have changed to what we say in his life time???? I don’t so. From teachings of Christ we see how faith only matter. What I trying to say is you can run away from yourself and no one van better represent you more than you yourself.
The discussion here misses its objective. We would have discouraged harmful cultures those do not contributes to the existence of the society and promote those promote the good of the society not just how Christians should not contextual culture. Such discussion may disrupt the basement of the society and should be discussed at intellectual level before saying in open. I am not against anyone but this is who are and so can not be disproved from personal institutions without full extent scientific analyses. I am, I respect my culture more than anyone and I am and will be a christian always.