Let Justice be done, though the heavens fall
ከዛሬ 248 ዓመታት በፊት፡ በ1772 ማንስፊልድ የተባለ እንግሊዛዊ ዋና ዳኛ አንድ አጣብቂኝ ጉዳይ (ኬዝ) ይገጥመዋል፡፡ አንድ ጀምስ ሶመርሴት የተባለ ከአፍሪካ ተይዞ የሄደ ባሪያ በእንግሊዝ ሕግ መሠረት ነፃነት እንዲሠጠው ፍ/ቤት ይቀርባል፡፡ የባሪያው ባለቤት(አሳዳሪ) ደግሞ ሶመርሴትን ወደ ጃማይካ ልኮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተከሳሹ ከጌታው አምልጦ ነው ሕግ ፊት የቆሜው፡፡
ዳኛው በዚህ ጉዳይ ላይ ረጅም ጊዜ ወስዶ ማሰላሰል ጀመር፡፡
የጉዳዩ ውስብስብነት እንዲህ ይመስላል፡፡
1ኛ፡ ዳኛው የባሪያውን ነፃነት ከልክሎ ለጌታው አሳልፎ ቢሰጥ፣ የባሪነት ንግድ በእንግሊዝም ምድር ሕጋዊነትን ይጎናጸፋል፡፡ የባሪያ ንግድን በሕጋዊ መልክ መፍቀድ ደግሞ ብዙ የሕግንና የፍትህ መርሆችን ድምጥማቱን ያጠፋቸዋል፡፡ ውጤቱ ደግሞ ብዙ ማህበራዊና ሕጋዊ ቀውሶችን የሚያስከትል ይሆናል፡፡
የእንግሊዙ “common law” እንዲህ የሚል ነው፡- “the common law takes no notice of negroes being different from other men. By the common law no man can have a property [interest] in another …” ሕጉ ጥቁሮች ከሌሎች ሰዎች የሚለዩበት ምንም ነገር አይመለከትም፣ በሕጉ መሠረት ማንም ሰው ሌላኛውን ሰው የራሱ ንብረት ማድረግ አይችልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሕጉ መሠረት ማንም ሰው ወደማይፈልገው ቦታ/አገር ተገድዶ መሄድ የለበትም የሚል ነው፡፡
ይህ ማለት ሕጉ በነጮችና በጥቁሮች መካከል ልዩነት የማያደርግ ነው፡፡ በተጨማሪም አንድን ሰው ባሪያ አድርጎ መግዛትም የሚከለክል ነው፡፡ በዚህ መሠረት ባሪያው ነፃነቱን የጠየቀው በዚህ ሕግ መሠረት ስለሆነ ይህንን መብት መከልከል ከሕጉ በተፃራሪ መቆምን ያመለክታል፡፡ እንዲሁም ሰውን አስገድዶ ወደማይፈልገው አገር መላክ ሌላ የሕግ ጥሰት ነው፡፡
2ኛ፡- ዳኛው በሕጉ መሠረት ለባሪያው ነፃነቱን ቢሰጥ ውሳኔው ብዙ የኢኮኖሚ ኪሳራን የሚያስከትል ይሆናል፡፡ በወቅቱ በእንግሊዝ ምድር 15,000(አሥራ አምስት ሺህ) የሚጠጉ ባሪያዎች እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ የእያንዳንዱ ባሪያ ዋጋ ቢያንስ £50 ይሆናል፡፡ የባሪያ ንግድ በሕግ ቢታገድ እንግሊዝ ባጭሩ ከ£700,000 sterling (sterling፡ የእንግሊዝ መገበያያ ገንዘብ) በላይ ትከስራለች ማለት ነው፡፡ ባሪያ ማሳደርን የሚፈቅደው የቅኝ ገዢዎች ሕግም መደምሰስ ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ ከ15ሺህ በላይ ባሪያዎች (ጥቁሮች) ብለቀቁ የሚያስከተለው ማህበራዊ ጫናም ሌላ ስጋት ነው፡፡
ዳኛው መዶሻቸውን አነሱ፣ “”If the parties will have judgment, fiat justitia, ruat coelum”7-let justice be done, though the heavens may fall.” ብለው የሚከተለውን ቃል አስተላለፉ፡-
“The state of slavery is of such a nature, that it is incapable of being introduced on any reasons, moral or political; but only positive law, which preserves its force long after the reasons, occasion, and the time itself from whence it was created, is erased from memory: it’s so odious, that nothing can be suffered to support it, but positive law.”
በአጭር ቃል፡- ቅኝ ገዢዎች የሚያቀነቅኑት ባሪያ ማሳደር የሚፈቅደው ሕግ በምንም ምክንያት (በፖለቲካዊም ሆነ በሞራል)፣ ተቀባይነት የለውም፣ እሱን ለማስጠበቅ ሲባል ምንም ዋጋ መከፈል የለበትም የሚል ነው፡፡
ደኛው ሲቀጥሉ፡
“…I cannot say this case is allowed or approved by the law of England; and therefore, the black must be discharged”
ስለዚህ ሶመርሴት ነፃ ይሂድ ተባለ፡፡
የሶመርሴት ነፃ መለቀቅ ለብዙ ባሪያዎች የነፃነት ትግል መቆስቆሻ ምክንያት ሆነላቸው፡፡ ሶመርሴትም ነጻነቱን ከተቀዳጀ በኋላ በተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ውስጥ ላሉ የሰው ልጆች ነፃነታቸውን እንዲያገኙ ትግል ጀመረ፡፡
ሰሞኑን አንድ ጥቁር አሜሪካዊ ባደባባይ በነጭ አሜሪካዊ ፖሊስ በግፍ ሲገደል አይተን አዝነናል፣ ተቆጥተናልም፣ ዓለም ሁሉ ተመሳሳይ ስሜት አንጸባርቋል፡፡ ግና ከሟቹ ጋር ምንም ዝምድና የሌለን ሰዎች ምን አስቆጣን?
የሰው ልጅ “የሰው ልጅ” በመሆኑ ብቻ በውስጡ ከታተሙ ስሜቶች መካከል አንዱ ፍትሕ ፍለጋ ነው፡፡ ይህ ከፈጣሪ ጋር የምንጋራው ባህሪይ ይመስለኛል፡፡
ፍትሕ ከሚጓደል ሰማይ ቢወድቅ ይሻላል!
ታርኩን ለማወቅ የምትፈልጉ እነዚህ ዶክሜንቶችን አንብቡ፡-
- Paul Finkelman: Let Justice Be Done, Though the Heavens May Fall: The Law of Freedom
- William M. Wiecek፡ Somerset Lord Mansfield and the Legitimacy of Slavery in the Anglo-American World.