<strong>ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ የተሰኘ ድርጅት በካራት ከተማ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ </strong>

ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ የተሰኘ ድርጅት በካራት ከተማ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ

ለህክምና ቡድኑ በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና በባህል አባቶች አቀባበል ሲደረግ

መቀመጫውን እስራኤል አገር ያደረገውና ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ በመባል የሚታወቀው ክርስቲያናዊ የተራዶ ድርጅት፣ በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ነጻ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች አመለከቱ።

የድርጅቱ ከፍተኛ የህክምና ቡድን ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ካራት ከተማ በገቡበት ወቅት የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው፣ የዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አስታውቋል።አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ አንዳንድ ታሪካዊ ቦታዎችንም ጎብኝተዋል።  

ከትላንት እሑድ ህዳር 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት በካራት ጤና ጣቢያ ህክምናውን እየሰጡ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ቢያንስ 10 ሺህ ያህል ታካሚዎች የአገልግሎታቸው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ድርጅቱ በካራት ከተማ ሊሰጥ ያለውን የህክምና አገልግሎት የሚያስተዋውቅ ማታወቂያ

በአምስቱ ቀናት የሚከናወነውን ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ለመድኃኒቶች፣ ለህክምና መገልጊያ ቁሳቁሶችና ለሌሎች አስፈላጊ መሣሪያዎች በተቋሙ በኩል ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉም ተገልጿል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ከመስከረም 8-15 ቀን 2015 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ተመሳሳይ ነጻ የህክምና አገልግሎት መስጠቱ በወቅቱ በደቡብ ራድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት መዘገቡ ይታወሳል።   

ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ በጌዴኦ ዞን የህክምና አገልግሎት ሲሰጥ

ጄዊሽ ቮይስ ሚኒስትሪስ መቀመጫውን በእስራኤል አገር ያደረገ ክርስቲያናዊ ምግባረ ሰናይ ተቋም ሲሆን፣በዓለም ዙሪያ አይሁዶች ባሉባቸው አገሮች በተለይ ለአይሁዶች ወንጌልን ማሠራጨትና ከዚሁ ጎን ለጎን የበጎ አድራጎት ተግባራትን በመፈጸም የሚታወቅ የተራዶ ድርጅት ነው።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *