<strong>የኮንሶ ልማት ማህበር ከጂ አይ ዚ ባገኘው ድጋፍ በአማሮ ልዩ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መሥራቱን አስታወቀ </strong>

የኮንሶ ልማት ማህበር ከጂ አይ ዚ ባገኘው ድጋፍ በአማሮ ልዩ ወረዳ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መሥራቱን አስታወቀ

አቶ ደረሰ ቆጫና – በኮንሶ ልማት ማህበር የጂ አይ ዜድ ፕሮጀክት አስተባባሪ

የኮንሶ ልማት ማህበር ጂ አይ ዜድ ከተሰኘ ምግባረ ሰናይ ድርጅት ባገኘው ድጋፍ፣ በአማሮ ልዩ ወረዳ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችንና የማህበርሰብን የኑሮ ማሻሻያ ሥራዎችን መሥራቱን፣ በኮንሶ ልማት ማህበር የጂ አይ ዜድ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ደረሰ ቆጫና አስታወቁ።

እንደ ፕሮጀክት አስተባባሪው የመረጃ፣ በጂ አይ ዜድ ፕሮጀቱ ለማህበረሰቡ ከተሠሩ ሥራዎች መካከል የተዳቀሉ የማንጎና የአቮካዶ ችግኝ አቅርቦት፣ የንብ ማነብ ሥራዎች፣ በችግኝ ማፍላት ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶችን መደገፍና ከ10 ኪሎ ሜት በላይ ርዝመት ያለው የኮንሶ እርከን ሥራ ተግባራዊ የማሳያ ፕሮጀክት ይገኙበታል ብለዋል።

የላቀ ተሳትፎ ላደረጉ የማበረታቻ ሽልማት ሲሰጥ

በተጨማሪም ለአካባቢ ጥበቃ፣ ልማትና ሌሎች ጉዳዮች የሚሆኑ የውሃ ፓምፖች፣ የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎች፣ የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎችና የተለያዩ የአታክልትና ፍራፍሬ ዘሮች ለኅብረተሰቡ መሠራጨቱንና ለደን ልማት ሥራ ከ40 ሺህ በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውን የፕሮጀቱ አስተባባሪ ጨምረው ተናግረዋል። ኮንሶ ልማት ማህበር የጂ አይ ዜድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ በሆኑ የአማሮ ልዩ ወረዳ የአልፋጮና አቡሎ ቀበሌዎች የተሻለ ሥራ ለሠሩት የጂ አይ ዜድ ተወካይ በተገኙበት የዕውቅና ሽልማት መስጠቱንም አስታውቋል። በዕውቅናና ሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ቀበሌ ነዋሪዎች የልማት ሥራውን አድንቀው ቀጣይነት እንዲኖራቸው መጠየቃቸው በልማት ማህበሩ መረጃ ተመልክቷል።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *