<strong>ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ </strong>

ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

አቶ ግርማ በሌ – አዲሱ የካራት ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ

ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ያሉበትን ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመቅረፍ፣ በህብረተሰቡ የሚቀርቡበትን ቅሬታዎች ለማስወገድ ችግሮቹን ለመቅረፍ እየሠራ መሆኑን፣ አዲሱ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ግርማ በሌ ለዞን ኮሚዩኒኬሽን መሥሪያ በሰጡት መረጃ አስታወቁ።

የመብራት መቆራረጥ፣ የሆስፒታሉ የውሃ መሥመር ብልሽት፣ የመድኃኒት አቅርቦት እጥረትና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶች ሆስፒታሉ ላይ ቅሬታ ከሚቀርብባቸው ቀዳሚዎቹ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ።

በተለይም የመድኃኒት አቅርቦት እጥረትና የአንዳንድ ባለሙያዎች የሙያ ሥነ ምግባርን ተከትሎ አገልግሎት መስጠት አለመቻል፣ ተገልጋይ ኅብረተሰቡ ከተማረረባቸው ችግሮች ዋነኞቹ ናቸው።

አዲሱ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ይህንን ሁኔታ ለመለወጥና የሆስፒታሉን ስም ለማደስ እየሠሩ መሆኑን ማስረዳታቸው ተገልጿል።

የሆስፒታሉን የመድኃኒት እጥረት ለመቅረፍ፣ ከዚህ በፊት እንቅፋት የሚሆኑ አንዳንድ ቢሮክራሲያዊ አሠራሮችንም ለማስተካከል ጥረት መደረጉንና ከዚህም የተነሳ የሆስፒታሉን የመድኃኒት ክምችት መጨመር መቻሉን ኃላፊ ተናግረዋል።

የካራት ሆስፒታል የመድኃኒት ግምጃ ቤት

የሆስፒታሉን የውሃና የመብራት ችግሮችንም በመቅረፍ የተባላሸውን የሆስፒታሉን ገጽታ መልሶ ለመገንባት ጥረቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም አቶ ግርማ፣ ለኮሚዩንኬሽን መሥሪያ ቤት በሰጡት መረጃ አስረድተዋል። ካራት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በኮንሶ ዞን ደረጃ አንድ ለናቱ የሆነና ለአጎራባችን ህዝቦች ጭምር አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም፣ በተለያዩና ዘርፈ ብዙ በሆኑ አስተዳደራዊ ችግሮች ምክንያት ለረጅም ጊዜ በኅብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲቀርብበት የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *