ባህል ና ክርስቲና

ባህል ና ክርስቲና

Tesfaye Chenfa: Student at Jimma university school of medicine

ሰሞኑን የኮንሶን ባህል ለማስተዋወቅ የምናደርገውን ጥረት አብዛኛው ተከታዮቻችን በበጎ የተመለከቱት ብሆንም አንዳንድ ክርስትያን ወገኖቻችን ግን እንዴ ጥሩ እንቅስቃሴ አልተመለከቱትም ። ብዙዎቻችን ክርስትያኖች ብንሆንም ለምንድነው ይሄ የሀሳብ ልዩነት በመካከላችን የተፈጠረው ?? ክርስትና እና ባህል እንዴት ነው መተያየት ያሉባቸው ? የክርስትና አስተምሮ ባህልን እንዴት ይመለከተዋል ?? ምን ምን አመለካከቶች አሉ?? የምለውን በጥቅቱ እንመልከት ።

Richard niebuhr ”Christ and culture” በሚለው መጽሐፉ ላይ በ5 መንገድ የክርስትና እና የባህልን ግንኙነት አስቀምጧል ። ይህ ሰው ክርስትና እና ባህል በ አፍርካውያን ዘንድ እንዴት ይታያል የምለውን ነው ለማየት የሞከረው ።

1 Christ against culture

በዚህ አስተሳሰብ ያሉት ክርስትናን ካለው ና ከነበረው ባህል ሌላ አማራጭ ባህል አድርገው ይመለከቱታል ። በዝህ አመለካከት ክርስትናን የተቀበለ አንድ ግለሰብ ወይ ክርስቶስን ይቀበላል ወይስ ደግሞ ያለው አማራጭ በነበረበት አረማው አለም (paganism) መቆየት ነው ። በዚህ አስተሳሰብ ጊዜ ክርስትና እንዴ ባህል አጥፍ እና አዲስ የባህል ምንፍቅና ነው የሚወሰደው ።

አብዛኛዎቹ የሰሜን አትላንትክ እና የአፍርካ ሚስዮናውያን ናቸው ቀዳሚ የዚህ ሀሳብ አራማጆች ። ክርስትና ማለት ባህል በሌለበት አካባቢ የሚኖር ሃይማኖት ስላልሆነ ከባህል በጸዳ መንገድ ክርስቲናን ከባህል ለይቶ ንጹህ ወንጌል ብቻ መስበክ ወይ ማስመሰል ነው ወይስ የማይቻል ነው ።

ክርስትያኖች እኮ የባህላቸው ውጤቶች ናቸው ። አንድ ክርስትያን አንድን ኢ አማኒ ወደ ሀይማኖቱ ለመጨመር የሚነሳው ከራሱ የባህል ዳራ በመነሳት በማህበረሰባዊነት እና በትምህርት ካከማቸው ቋንቋ እና የባህል መሳሪያዎችን ይጠቀማል ። በተግባር ስታይ አንድ ሚስዮናው ክርስቶሰሽን ከባህል ተቃራኒ አድርጎ ካቀረበ የራሱ ባህል ና ቀጣይ ክርስትና የሚቀበሉ ሰዎች ባህል ጋር ግጭት ይከሰትበታል ይሄም ሌላ ማኅበራው ቀውስ ያመጣል ።

2 The Christ of culture

በለላ መልኩ አንዳንድ ክርስትያኖች ክርስቶስን የህዝቦች ን ሃይማኖታው እና ባህላዊ ቅርስ ለማስቀጠል ወይም ለማረጋገጥ የመጣ የግዜ ብሔር ልጅ ነው ብለው ይመለከቱታል ። እነዚህ ሰዎች ወንጌል የባህል ሙላት እነጂ የባህል ስጋት አይደለም ብለው ይመለከታሉ ለዚህም የተራራውን ስብከት (ማት :5_7) ያነሳሉ ። ክርስቶስ ”ለሁሉም ባህሎች የሚሆን” ሲሆን ሰዎች በየራሳቸው ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ወጎች አውድ ውስጥ እንድገነዘቡ እና እንዴ እግዚአብሔር ፍቃድ እንድኖሩ ይረዳቸዋል ።

ስለዚህ ክርስቲና በባህል አንድ ወጥ ልሆን አይችልም ። በሐዋርያት ግዜ የነበሩ አብያተ ክርስቲያናት ይህንን በ ክርስቶስ እና በባህል መካከል ያለውን ግንኙነት ቀድመው ወስደዋል ።ምንም እንኳን የአይሁድ-ክርስቲያን እና የሄለናዊ-ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እርስ በእርሳቸው ኅብረት ቢኖራቸውም እያንዳንዱ ልዩ ባህላዊ ልዩነቱን እንደያዘ ቆይቷል። አንድ ሰው ለምሳሌ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ጉልህ ልዩነቶችን መጠበቅ አለበት።

3 Christ above culture

ይህ አስተሳሰብ በክርስትና እና በባህል መካከል ያለውን ግጭት የሚያስቀር ተደርጎ ይታሰባል ። የዚህ ሀሳብ ባለቤት ቅዱስ አውግስጥኖስ ነው

”በሰማያዊና በምድራዊ ከተሞች መካከል ያለውን ልዩነት ስናደርግ ክርስትና በሰማያትና በወደፊት ባለው “መዳን*” ላይ ያተኮረ ከብዙ ዘመናት ተሻጋሪ ይሆናል።”ክርስትና በሰማያው ከተማ የሚገኝ ሲሆን ባህል በምድራው ከተማ የምገኝ ይሆናል ።

በተግባር, እንዲህ ዓይነቱ ሃይማኖታዊነት ለአሁኑ ፍላጎቶች ጋር ለማስማማት አስቸጋር ይሆናል ።

4 Christ and culture in paradox

በዝህ ጎራ ያሉት ክርስቶስን ከባህል ጋር ይለዮታልም ያስማሙታልም ።

”ቤተክርስቲያን በአለም ውስጥ ትገኛለች, ምንም እንኳን የዓለም ባትሆንም ”- የፕሮቴስታንት ተሐድሶ በተለይም የሉተር* አመለካከት ነው ።

ችግሩ ክርስቶስ ሕልን በመደገፍ ወይም በመቃወም የሚገለጽበትን ሁኔታ በተመለከተ ግልጽነት የጎደለው ነው።በዘመናውው የክርስትና አገልግሎት ይሄንን የምወስኑት ምሶናውያን ናቸው ።እነዝህ ምሶናውያን ደግሞ በአጠቃላይ ለባህላቸው ካላቸው ቀናእነት የተነሳ አድሎአው ይሆናሉ ። ወንገል ለመስበክ በደረሱበት እና እንግዳ በሆኑበት ያለውን ባህል ይቃረናሉ ።ነገር ግን የራሳቸውን ባህል ስቃረኑ አይታዩም ።ያ ነው ትልቁ ችግር ።

5 Christ the transformer

እነዝህ ክርስቲያኖች ክርስቶስን እንዴ ባህል ቀያሪ ይረዱታል ። ለዝህም ራዕይ 21:5 ይጠቅሳሉ ። መቀየር ለክርስቲያኖች መንገዳቸውን ቀይረው አድስ ፍጡራን እንድሆኑ እንዴ ፈተና ይቆጠራል ።የተቀየሩ ፈተናውን ያለፉ ይሆናሉ ።

የጳውሎስ መለወጥ ብዙውን ጊዜ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል. ከክርስቲያኖች “አሳዳጅ” ወደ “ፍጹም”ክርስትና ተለውጧል። ሆኖም “ለውጡ” ቀደም ሲል የነበረውን የሕይወት መንገድ እንደማይተወው ይገምታል ።ሆኖም አዳድስ ግንዛበዎችን እና ቁርጠኝነት ያስፈልገው ነበር ።ስለዝህ በነዝህ ነገሮች ማለፉ አስፈላጊ ነበር ።

በተግባር, የለውጥ ጽንሰ ሀሳቦች ብዙውን ጊዜ ከሚስዮናውያን ባህል የተወሰዱ ናቸው; ከዚያ የተገኘው ለውጥ ከማንኛውም ሌላ የመሰብሰብ ሂደት * እና ውጤት ጋር ሊወዳደር ይችላል። በአፍሪካ ውስጥ፣ በቅኝ ግዛት ስር ያሉ አብዛኛዎቹ የባህል ለውጦች እና የሚስዮናውያን ሞግዚቶች እንደዚህ አይነት ናቸው። ስለዚህ ብዙዎቹ የአፍሪካ ልሂቃን ለዘመናዊው የክርስቲያን ሚሲዮናውያን ድርጅት አፍሪካውያን በዘመናዊነት ሰበብ ለደረሰባቸው የባህል መገለል ተጠያቂ አድርገዋል።

ይሄንን ጽሁፍ ያቀረብኩት ባህል ከክርስትና አንጻር እንደት መታዬት አለበት የምለውን ሀሳብ የሀይማኖት መምህራን መረዳታቸውን እንድያቀርቡልን እና የጠራ አስተሳሰብ እንድኖረን ለመጋበዝ ነው ።


1 Comment

  1. Yavello Nataye

    በባህል አውድም ውይይት ለመክፈት ስላቀረበው መነሻ ሐሳብ ላመሰግንህ ወዳለሁ። በስነ መለኮት ጥልቅ ዕውቀት ያላቸውም ሆነ ሌሎቻችንም የምንረዳውን በባህልና ክርስትና አንፃር እንድናጋራ እኔም አብረህ በትህትና ጠይቃለሁ። 🙏😇

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *