<strong>በኮንሶ ዞን የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ነው</strong>

በኮንሶ ዞን የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ እየተካሄደ ነው

በኮንሶ ዞን ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የኩፍኝ ክትባት በዘመቻ መልክ መሰጠት መጀመሩን የዞን መንግሥት የኮሚዩንኬሽን መሥሪያ ቤት አስታወቀ።

ክትባቱ አገር አቀፍ የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታን መከላከል ዘመቻ አካል መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በኮንሶ ዞን ውስጥ በሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች መጀመሩን፣ የዞን ጤና መምሪያ ጠቅሶ የኮሚዩኒኬሽን መሥሪያ ቤቱ በዘገባው አስታውቋል።

በክትባት ዘመቻው፣ ከዚህ በፊት መደበኛ ክትባት ያልወሰዱና ክባት መውሰድ ጀምረው ያቋረጡ ህጻናት ጭምር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ፣ የጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደይጋንቶ ኡርማሌ መናገራቸው ተገልጿል።

ከኩፍኝ ክትባት ዘመቻው በተጓዳኝ የሆድ ጥገኛ ትላትል፣ የምግብ እጥረት በሽታ፣ የዓይን በሽታ፣ የፊስቱላ ህመም ልየታና እግራቸው የተቆለመመ ህጻናትንም የመለየት ሥራ እየተሠራ መሆኑን፣ የክትባት ዘመቻው ተቆጣጣሪና በዞኑ ጤና መምሪያ የስነ ተዋልዶ ጤና ባለሙያ አቶ አራርሶ ጋሮ ተናግረዋል።

የክትባት ዘመቻውን ለማስጀመር የተለያዩ የዞን መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተገኝተው ማስጀመራቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ዘመቻው ከታኅሳስ 17 እስከ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥ ከዚህ በፊት በኮሚዩኒኬሽን መሥሪያ ቤት በኩል መገለጹ የሚታወስ ነው።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *