በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በምግብ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት በመፈጸም ለንጹሃን ሞት ምክንያት በሆኑ ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ ተበየነ

በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ በምግብ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት በመፈጸም ለንጹሃን ሞት ምክንያት በሆኑ ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ ተበየነ

በኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ሰገን ከተማ፣ በአንድ ምግብ ቤት ላይ ቦምብ በመወርወር ለንጹሃን ዜጎች ህይወት ማለፍና ለአካል ጉዳት እንዲሁም ለንብረት ውድመት ምክንያት በሆኑ ግለሰቦች ላይ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከ24 አመት ጽኑ እሥራት እስከ ሞት ቅጣት መበየኑን፣ የዞን መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን መሥሪያ ቤት አስታወቀ።

በክስ መዝገቡ በ1ኛ ተከሳሽነት በቀረበው በአቶ ሰለሞን ከበደ ሀብቴ ላይ ፍርድ ቤቱ የ24 አመታት ጽኑ እሥራት የበየነ ሲሆን፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሽ በሆኑት በአቶ ኦላታ ጅግና እና በአቶ ዳኜ ገቢኖ ላይ ፍርድ ቤቱ የሞት ቅጣት በይኗል።

አቅቤ ህግ የኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና ለ፣ አንቀጽ 58/1/ሀ እና አንቀጽ 539/1/ሀን በመጥቀስ በክሱ ለፍርድ ቤቱ እንዳብራራው፣ ከላይ ስሙ የተገለጸው አቶ ኦላታ ጀግና የተባለው 2ኛ ተከሳሽ፣ የህግ ምስክር ከሆኑት መካከል 7ኛው በተከራዬው ምግብ ቤት ላይ ቦምብ በመወርወር በወቅቱ በምግብ ቤቱ ውስጥ ሲመገቡ ከነበሩ መካከል አቶ በቀለ በየነ የተባሉ የወረዳው የጤና ባለሙያ ላይ በደረሰ ጉዳት ህይወቱ በቦታው ላይ ማለፉ ተገልጿል።

ወንጀለኞቹ የቦምብ ጥቃት ከማድረሳቸው በተጨማሪ በአካባቢው ላይ መቴሪየስ ከባድ የጦር መሣሪያ በመጥመድና ወደ ምግብ ቤቱ የተኩስ እሩምታ በመክፈት ጭካኔ በተሞላበት አኳኋን የጤና ባለሙያውን ህይወት ማጥፋታቸውና ሌሎችንም ማቁሰላቸው በአቃቤ ህግ ተብራርቷል።

በከባድ የግድያ ወንጀል፣ በከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እና በንብረት ማውደም የተከሰሱት 2ኛና 3ኛ ተከሳሾች በመሰወራቸው፣ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ሳይቀር ህግ ፊት እንዲቀርቡ ጥሪ የተደረገላቸው ቢሆንም፣ መቅረብ ባለመቻላቸው በሌሉበት የህግ ክርክሩ ተካሂዶ ሁለቱም የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል።

ሌላኛው ውሳኔ የተላለፈበት አንደኛ ተከሳሽ አቶ ሰለሞን ከበደ ሀብተ ሚካኤል በ24 አመት ጽኑ እሥራት እንዲቀጣ፣ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ምድብ ችሎት ውሳኔ አስተላልፏል። የቀድሞው የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን፣ ኮንሶ በዞን መደራጀቱን ተከትሎ ከፈረሰ በኋላ፣ አካባቢው ላይ የራሳችን “ልዩ ወረዳ ካልተሰጠን፣ አካባቢውን እናሸብራለን” የሚሉ ጽንፈኛ ሽብርተኛ ኃይሎች አካባቢው ላይ ተፈልፍለው፣ የኮንሶውን የሰገን ዙሪያ ወረዳ ለረጅም ጊዜ የጦር አውድማ ማድረጋቸው አይዘጋም። ይህንንም ተከትሎ በወረዳው አቶ በቀለ በየነን ጨምሮ የብዙ ወጣት ምሁራንና ባለሙያዎች ህይወት በእነዚሁ ሽብርተኛ ኃይሎች መቀጠፉም ይታወሳል።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *