ህወሓት ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታወቀ

ህወሓት ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታወቀ

ህወሐት ከመንግስት ጋር ለሚያደረግው የሰላም ንግግር ጌታቸው ረዳን እና ጀነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ያከተተ ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በድጋሚ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛው ቦታ ከህወሓት ጋር እንደሚደራደር መግለጹም ይታወሳል።

ህወሐት ትላንት ማምሻው “የትግራይ የውጭ ግንኙነት ጸ/ቤት” ብሎ በሰየመው መሥሪያ ቤቱ በኩል ባወጣው መግለጫ፣ የተሰየመው ተዳራዳሪ ቡድን ወደፊት በሚደረገው ድርድር “የትግራይን መንግስት” የሚወከል ስልጣን ተሰጥቶታለል ብለዋል።ህወሓት የተሰየመው ተደራዳሪ ቡድን በአጭር ጊዜ ወደ ድርድር ይገባል ብሏል።

በአፍሪካ ኅብረት ገለልተኝነት ላይ ጥያቄ ሲያነሳ የነበረው ህወሓት፣ በኅብረቱ ጥላ ስር በሚካሄደው ድርድር ያለ ቅድመ ሁኔታ እንደሚሳተፍ በመግለጫው ገልጿል። ከዚህ ባለፈም “ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር አፋጣኝና በጋራ ስምምነት ለሚደረግ ተኩስ አቁም ዝግጁ ነኝ” ብሏል በመግለጫው።

ህወሐት በሀገሪቱ ለተከሰተው አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው በሰላማዊ ውይይት ብቻ እንደሆነ እናምናለንም ብሏል።

በአዲሱ አመት ግጭቱን አቁመን ለሰላም እድል በመስጠት የሰላም እና ብልጽግና መንገድ እንጀምር ያለው ህወሐት፤ “በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ሂደት አስተማማኝ እንዲሆን” እንጠብቃለን ብሏል።

የሰላም ሂደቱ በሁለቱም ወገን ተቀባይነት ያላቸው ሸምጋዮች እንደሚጨመርና ፤በሂደቱ በሁለቱም ወገኖች መካከል የእርስ በርስ መተማመን እንዲፈጠር የሚያግዙ፣ አፈጻጻምን የሚከታተሉ እንዲሁም አስፈላጊውን መመሪያና ምክር የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እንዲሳተፉም እንደሚፈልግ ህወሓት ገልጿል።

በፌደራል መንግስቱ እና በህወሓት መካከል የነበረው ጦርነት ለወራት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ በድጋሚ ሊቀሰቀስ ችሏል፤ ጦርነቱን ለ3ኛ ጊዜ የቀሰቀሰው ህወሐት ነው ብሎ የፌዴራል መንግሥት ሲከስ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግስት በድጋሚ ጦርነት ከመቀስቀሱ በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛው ቦታ ከህወሓት ጋር እንደሚደራደር መግለጹም ይታወሳል።

ህወሓትም በተመሳሳይ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ቢገልጽም ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ላይ እምነት እንደሌላው ሲገልጽ ቆይቶ ነበር።አሁን ግን ያለ ቅድመ ሁኔታ በአፍሪካ ኅብረት መሪነት በሚደረገው ድርድር ላይ ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ መሆኑንና ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም በመግለጫው ጠይቋል።

ከቀናት በፊት የህይወት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ኃይል፣ ጣልቃ ገብቶ ጦርነቱን እንዲያስቆም መጠየቃቸውን ቢቢሲ መዘገቡ አይዘነጋም።

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *